Women working on seedlings for a Nature-based solutions project in Dire Dawa, Ethiopia

SUNCASA

SUNCASA የአየር ንብረት ለውጥን ለመላመድ በከተማ በተፈጥሮ ላይ የተመሠረቱ ተግባራትን (NbS) የማስፋፋት መርሐ ግብር ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገራት በኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ እና ደቡብ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን  አደጋን የመቋቋም፣ የሥርዓተ ጾታ እኩልነት፣ ማሕበራዊ አካታችነት እና የብዝኀ ሕይወት ጥበቃን ለማሳደግ ያለመና በ3 ዓመት የሚተገበር ፕሮጀክት ነው።

SUNCASA በድሬዳዋ (ኢትዮጵያ)፣ ኪጋሊ (ሩዋንዳ) እና ጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ) ከተሞች ከባድ የጎርፍ አደጋ ሥጋት ባለባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ 2.2 ሚሊዮን ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። በፓርትነሪንግ ፎር ክላይሜት ፕሮግራም አማካኝነት በግሎባል አፌርስ ካናዳ የሚደገፍ ሆኖ በዓለም አቀፍ የዘላቂ ልማት ኢንስቲትዩት እና በወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት የሚተገበረው የSUNCASA ፕሮጀክት  አገርበቀል ድርጅቶች ጋር በአጋርነት የሚተገበር ነው። የፕሮጀክቱ ሥርዓተ-ጾታን ያማከሉ የNbS መፍትሄዎችን የላይኛው የተፋሰስ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋምና ለመጠበቅ በጥምር ግብርና ደን ልማት፣ በደን ተከላ እና ደን መልሶ ማልማት፣ ሞዴል የማህበረሰብ ፓርኮች እና የከተማ ዛፍ ተከላን  ያካትታሉ።