Juskei river in Alexandra Township, Johannesburg. SUNCASA. Photo by CHA

ጆሃንስበርግ

በጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪካ ሱንካሳ የላይኛው የጁክስኪ ወንዝ ተፋሰስ መልሶ ልማትን ለማከናወን፣ የጎርፍ መጠንን ለመቀነስ፣ የከተማ ሙቀት አስተዳደርን ለማሻሻል፣ የውሃ ዋስትናን ለማሻሻል፣ ኑሮን ለመደገፍ፣ አረንጓዴ አካባቢዎችን ለማስፋትና ብዝኃ ሕይወትን ለመጠበቅ ድጋፍ ያደርጋል። በነዚህ ሥርዓተ-ጾታን ያማከሉና ተፈጥሮ ላይ መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎች 1.045 ሚሊዮን ሰዎች ተጠቃሚ የሚደረጉ ሲሆን በተለይ በዋናነት ለተቸገሩ ወገኖች ወደ 1,000 የሚጠጉ የአረንጓዴ ሥራ እድሎች ይፈጠራሉ፡፡

በጆሃንስበርግ በወንዞች ሥርዓት ውስጥ ያሉ ባዕድ ወራሪ ዝርያዎች የከተማዋን የውሃ ዋስትና አደጋ ላይ ጥለውታል፣ የጎርፍ አደጋን ጨምረዋል እንዲሁም በአካባቢ ብዝኃ ሕይወት ላይም ተጽዕኖ በማሳደር ላይ ናቸው። በጁክስኪ ያሉ ማኅበረሰቦች በተለይም ውስን የመላመድ አቅም ያላቸው ዝቅተኛ ክፍሎች ከሙቀት መጨመርና በከተሞች ከሚስተዋለው የከፍተኛ ሙቀት ደሴት ተፅእኖዎች ጋር በመታገል ላይ ናቸው፡፡

የጁክስኬይ ተፋሰስ ጥቅጥቅ ብለው የተገነቡ መደበኛና ኢ-መደበኛ የመኖሪያ አካባቢዎችን፣ የግብርና ቀጣናዎችንና የችርቻሮ ማዕከሎችን ያጠቃልላል። በእነዚህ ክልሎች ውስጥ ያሉ ኢ-መደበኛ ሰፈራዎች በተለይ ለጎርፍ ተጽእኖዎች፣ ለተበላሹ መሠረተ ልማቶችና ለዕቃ መጥፋት ተጋላጮች ሲሆኑ ጎርፍ በሚከሰትበት ወቅትም ከጤና ጋር የተያያዙ ስጋቶች የተለመዱ ናቸው።

ሱንካሳ በአካባቢው ከሚገኙ አጋሮች ጋር በመተባበር የከተማዋን የውሃ መስመሮች የሚዘጉ ባዕድ ወራሪ ዝርያዎችን ለማስወገድ፣ የወንዙን ​​ዳርቻ መልሶ ለማልማት፣ የከተማ ሙቀትን ለመቆጣጠርና የውሃ ዋስትናን ለማሳደግ ቅድሚያ ይሰጣል። በተጨማሪም  ሥራዎቹ የሀገር በቀል ዕፅዋትንና ዛፎችን ለማስፋፋት አረንጓዴ ቦታዎችን በዛፍ ተከላና አትክልትና ፍራፍሬ ማልማት ሥራዎች ላይ ያተኩራሉ።

ተፈጠሮን መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎች እንቅስቃሴዎች በጁክስኪ ወንዝ ተፋሰስ

SUNCASA - Joburg Watershed vertical