SUNCASA | "BE THE RIVER MESSAGE" on a wall next to Jukskei River at Victoria Yards, Johannesburg.

ስለ

SUNCASA በድሬዳዋ (ኢትዮጵያ)፣ በኪጋሊ (ሩዋንዳ) እና በጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ) የአየር ንብረት ለውጥ መላመድንና የብዝኃ ሕይወት ጥበቃን ለማጎልበት በየአካባቢዎቹ ለተለዩ ፍላጎቶችና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ጉዳዮች በቀጥታ ምላሽ በመስጠት እየሠራ ይገኛል። ለተፋሰስ ጥበቃና መልሶ ልማት ሥርዓተ-ጾታን ያማከሉና ተፈጥሮ ላይ መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎችን (NbS) ተግባራዊ የሚያደርገው ይህ ዕቅድ የጎርፍ መጥለቅለቅን ጨምሮ ከተሞች ከአየር ንብረት ጋር ተያያዥነት ያላቸው በርካታ ስጋቶችን መቋቋም እንዲችሉ አቅማቸውን ለማጎልበት ያለመ ነው።

ይህ ሥርዓተ-ጾታን ያማከለ NbS ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ 2.2 ሚሊዮን አከባቢ ሰዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርግ ይሆናል። በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በሚተገብራቸው ዘላቂ የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ምክንያት 7 ሚሊዮን የሚሆኑ ነዋሪዎች ኑሯቸው የሚሻሻል ከመሆኑም ባሻገር ከተማዋ የውሃ እጥረትንና ሙቀትን እንዲሁም የመሬት መንሸራተትንና የአፈር መሸርሸርን ለመቋቋም ያላት አቅም ይጨምራል።


SUNCASA ተግባራዊ ከሚያደርጋቸው ተፈጥሮን መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎች መካከል በድሬዳዋና በኪጋሊ የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ ማልማት፣ በኪጋሊ የተራቆቱ የከተማ ደን መሬቶችን መልሶ ማልማትና መልሶ ማቋቋም እንዲሁም በጆሃንብሰርግ የጁክስኬይ ወንዝ (put an English name here) ተፋሰስን ወረው የሚገኙ መጤና ተዛማች የዕጽዋት ዝርያዎችን ማስወገድ ይገኙበታል። ከመልሶ ማልማት ተግባራት ጎን ለጎን SUNCASA የተፋሰስና ረግረጋማ አካባቢዎችን የመልሶ ማልማት ሥራ የሚያከናውን ሲሆን የከተማ የዛፍ ሽፋንን በመጨመር በሦስቱም የከተማ የሙቀት ችግርን ለመፍታት ያስችላል።

የምንከተለው ዘዴ

የSUNCASA ስኬት በሦስት ወሳኝ ሐሳቦች ላይ የተመሠረተ ነው። በመጀመሪያ ስለአየር ንብረት ለውጥ ተወራራሽ የሥርዓተ-ጾታ ተጽእኖዎች የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖርና ሥርዓተ-ጾታን ያማከሉና ተፈጥሮ ላይ መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎችን በተመለከተ ግልጽነት እንዲዳብር ያደርጋል። ሁለተኛው በየአካባቢዎቹ ያሉ አጋር አካላት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዙ ስጋቶችን ለመቅረፍ ተፈጥሮ ላይ መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎችን መጠቀም ውጤታማና ከወጪም አንጻር አዋጭ መንገድ መሆኑን የሚቀበሉ መሆናቸው ነው። ሦስተኛው ደግሞ የማዘጋጃ ቤት ኃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት አሁን ያሉት የአስተዳደር ማዕቀፎች ሥርዓተ-ጾታን ያማከሉና ምላሽ ሰጪ እንዲሆኑ ማስተካከያዎችን ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸው ነው።

ግቦቻችን

የSUNCASA ተነሳሽነት የሚከተሉት ናቸው፡-

  • የጎርፍ አደጋን ለመቀነስና አስተማማኝ የውሃ አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ የወንዞችን ተፋሰስ መልሶ በማልማትና በማደስ ሥርዓተ-ጾታን ያማከሉና ተፈጥሮ ላይ የተመሠረቱ መፍትሔዎችን ማዳበርና መተግበር
  • ሴቶችና በቂ ውክልና የሌላቸው ቡድኖች በአየር ንብረት መላመድ ውሳኔ አሰጣጥ፣ ዕቅድ፣ አቅርቦትና ክትትል ላይ  የሚገጥማቸውን እንቅፋት በማስወገድ የሥርዓተ-ጾታ እኩልነትንና ማኅበራዊ ፍትሕን ማጎልበት
  • ዘላቂ መተዳደሪያ እንዲኖር ማድረግና የአካባቢዎቹን ብዝኃ ሕይወት ማሰደግና መጠበቅ
  • የአረንጓዴ የሥራ ዕድሎችን መፍጠር
  • አረንጓዴ የሕዝብ የጋራ ቦታዎችን በማልማት የማኅበረሰቡን ደኅንነት ማሻሻል
     

የኛ ቡድን

Headshot of Ben Simmons

Benjamin Simmons

Senior Director, Economic Law and Policy

Todd Gartner, WRI

Todd Gartner

Director, Cities4Forests and Natural Infrastructure, WRI

Aklilu Fikresilassie, WRI - SUNCASA

Aklilu Fikresilassie

Director, Thriving Resilient Cities, WRI Africa; Representative of WRI in Ethiopia

Head shot of Alec Crawford

Alec Crawford

Director, Nature for Resilience

Alemakef Tassew, Urban Development Project Specialist, WRI Africa

Alemakef Tassew

Urban Development Project Specialist, WRI Africa

Amanda Gcanga, WRI Africa, Johannesburg, SUNCASA

Amanda Gcanga

Country Lead for Urban Water Resilience & Senior Urban Policy Analyst, WRI

Head shot of Ana

Ana Balanean

Policy Advisor, Gender Equality and Social Inclusion

Ayushi Trivedi, Gender Specialist, WRI

Ayushi Trivedi

Research Associate, Gender and Social Equity, WRI

Cesar Henrique Arrais

Cesar Henrique Arrais

Senior Communications Officer

Clare Blackwell, WRI - SUNCASA

Clare Blackwell

Research Analyst II, WRI

Daniela Facchini, WRI - SUNCASA

Daniela Facchini

Director, Global Operations and Program Management, WRI Ross Center for Sustainable Cities

David Uszoki

David Uzsoki

Lead, Sustainable Finance

dimple-roy-2019.jpg

Dimple Roy

Director, Water and Director, Manitoba Relations

Eden Tekele, WRI Africa - SUNCASA

Eden Takele

Engagement & Communications Specialist, Climate Program and WRI Ross Center for Sustainable Cities, WRI Africa

Hellen Wanjohi-Opil, WRI AFrica

Hellen Wanjohi-Opil

Resilience African Cities Lead, WRI Africa

Josephine Apajo, WRI - SUNCASA

Josephine Apajo

Planning, Monitoring and Evaluation Learning Manager, WRI Africa

IISD-DSC08219 - Liesbeth Casier for web.jpg

Liesbeth Casier

Lead, Public Procurement and Sustainable Infrastructure

Lisa Beyer, WRI

Lisa Beyer

Urban Water Infrastructure Manager, WRI

Lizzie Marsters, WRI

Lizzie Marsters

Environmental Finance Manager, Natural Infrastructure, WRI

lynn-wagner-2018.jpg

Lynn Wagner

Senior Director, International Environmental Governance

Marc Manyifika, WRI Africa

Marc Manyifika

Country Lead for Urban Water Resilience/Lead Spatial Planner for the program, WRI Africa

matt-small.jpg

Matthew TenBruggencate

Communications Manager

Meghan Stromberg, WRI

Meghan Stromberg

Urban Resilience Project Coordinator, WRI Ross Center for Sustainable Cities

Headshot of Michail

Michail Kapetanakis

Policy Advisor, Sustainable Infrastructure

Woman with curly hair wearing black and smiling

Nona Rogava

Project Manager

Pablo Lazo, WRI - SUNCASA

Pablo Lazo

Director of Urban Development, WRI Ross Center for Sustainable Cities

Bio photo of Richard Grosshans

Richard Grosshans

Lead, Bioremediation

Sadof Alexander

Sadof Alexander

Communications Manager, Cities4Forests, WRI

Head shot of Samantha Boardley

Samantha Boardley

Associate

Stefan-Jungcurt-2019.jpg

Stefan Jungcurt

Lead, SDG Indicators and Data

Tristan-Easton-2019.jpg

Tristan Easton

Senior Project Manager