SUNCASA | Volunteers planting a tree as part of the launch of the #MyTree community tree planting campaign in the Gasabo District on October 26, 2024. (Photo: Rwanda Young Water Professionals | SUNCASA)

ከተማን መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎች

የSUNCASA የተፋሰስ መልሶ ማልማትና አረንጓዴ ሥራ የአፍሪካ ከተሞች በአየር ንብረት ተጽእኖዎች በተለይም በጎርፍና በድርቅ ምክንያት የሚፈጠሩና እየተባባሱ የመጡ ተግዳሮቶችን የመቋቋም አቅምን ለማሳደግና የብዝኃ ሕይወትና የሥነ-ምህዳር ጤናን በማጠናከር የመሬትና የውሃ መራቆትን ለመቅረፍ ያለመ ነው።

በአፍሪካ ከሚገኙት ከተሞች ውስጥ ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑትለአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖ የተጋለጡ ሲሆኑ እነዚህ ስጋቶች በተለይ ከፍተኛ ተጋላጭነት ባለባቸው ማኅበረሰብ ዘንድ እጅግ ከባድ ናቸው። ተፈጥሮን መሠረት ያደረጉ መቋቋም ስልቶች/መፍትሔዎች (NbS) ለተሻሻለ መላመድና ብዝኃ ህይወት መጠበቅ አስተዋፅዖ እያደረጉ የአየር ንብረት አደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ወጪ ቆጣቢ የሆኑ ዘዴዎች በመባል ይታወቃሉ።

SUNCASA በድሬዳዋ (ኢትዮጵያ)፣ ኪጋሊ (ሩዋንዳ) እና ጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ) በፈጣን የከተሞች መስፋፋት፣ በአዲስ የአየር ንብረት አስተዳደር ሥርዓቶች፣ ደካማ መሠረተ ልማቶች፣ ደካማ ማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ችግር ባለባቸው ብዙ ሕዝቦች መኖር ምክንያት እየጨመረ የመጣውን የአየር ንብረት ተጋላጭነት ለመቅረፍ ያለመ ነው፡፡

የSUNCASA ለተፈጥሮ ምቹ ዕቅድ ዓላማው የመኖሪያ አካባቢዎችንና ግንኙነታቸውን እንዲሁም ሥነ-ምህዳራዊ ቅርፅንና ተግባርን ማሻሻል ነው፡፡ ለመልሶ ማልማትና ለአረንጓዴ ሥራዎች ሀገር በቀልና ለአከበቢ ተስማሚ፣ የተለያዩ፣ ከሥነ-ምህዳር ጋር የተጣጣሙና ሁለገብ ዝርያዎችን ይጠቀማል። እነዚህ ተግባራት ጎርፍና የመሬት መንሸራተትን ለመቀነስ እንዲሁም የአፈር መሸርሸርን ለመቆጣጠር የከተማ ሙቀትን ለመቀነስና ብዝኃ ሕይወትን ለመጠበቅ ይረዳሉ፡፡:

SUNCASA በየከተሞቹ ያሉ የማዘጋጃ ቤት አስተዳደሮችን፣ የአካዳሚክና የሲቪል ማኅበረሰብ አጋሮችን፣ የሴቶች ድርጅቶችንና ማህበረሰቦችን ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራትን የሚመለከት አውድ-ተኮር ተፈጥሮ ላይ መሠረት ያደረገ መፍትሔ በመንደፍ፣ በመተግበር፣ በመከታተልና በመደገፍ ያግዛል። SUNCASA የሀገር ውስጥ አጋር አካላት የአካባቢያዊ የአየር ንብረት መላመድ ግቦችን የሚያሳኩ ውጤታማ ተፈጥሮ ላይ መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎችን ለማቅረብ በሚያስችል ደረጃ የሠለጠኑና አቅም ያላቸው መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይሠራል።