SUNCASA | Volunteers planting a tree as part of SUNCASA launch in Kigali. November, 30, 2024 (Photo: William Bidibura | ARCOS Network | SUNCASA)

ኪጋሊ

SUNCASA በኪጋሊ ሩዋንዳ የጎርፍ አደጋን፣ የመሬት መንሸራተትንና የአፈር መሸርሸርን ለመቀነስ በታችኛው የኒያባሮንጎ ወንዝ ተፋሰስ ውስጥ ወሳኝ የሆኑ ንኡስ ተፋሰሶች መልሰው እንዲያገግሙ ያደርጋል። ፕሮጀክቱ የደን ልማትን፣ የደን መልሶ ማልማትን፣ ጥምር የግብርናና ደን ልማትንና የከተማን ዛፍ ተከላን ጨምሮ ሥርዓተ-ፆታን ያማከሉና ተፈጥሮ ላይ መሠረት ያደረጉ የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም የሚያስችሉ መፍትሔዎች (NbS) በማጣመር እነዚህን ስጋቶች በመፍታት የ975,000 ሰዎችን የመቋቋም አቅም ይጨምራል።

ኪጋሊ ባላት ወጣ ገባ የመሬት አቀማመጥና ፈጣን የከተማ መስፋፋት እየተባባሰ የመጣ አሳሳቢ የአየር ንብረት አደጋ በተለይም የጎርፍ መጥለቅለቅና የመሬት መንሸራተት አጋጥሟታል። በነዚህ የNbS መፍትሔዎች የሚተገበሩባቸው የኪኩኪሮ፣ ኒያሩገንጌና ጋሳቦ አውራጃዎች ብዙ ቤቶችን ለመሬት መንሸራተትና የታችኛውን ተፋሰስ አካባቢዎች ደግሞ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ያደረጉ ገደላማና ተዳፋት ቦታዎች አሏቸው፡፡

የSUNCASA ሥራዎች ከሀገር ውስጥ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በኒያባሮንጎ ወንዝ ተፋሰስ ውስጥ በጥምር የግብርናና ደን ልማት፣ በደን ልማትና በደን መልሶ ማልማት ወሳኝ የሆኑ ንዑስ ተፋሰሶችን መልሰው እንዲያገግሙ ያደርጋል። በተጨማሪም የመሬት ወረራዎችን በመቆጣጠር የወንዝ ዳርቻዎችን ባሉበት እንዲቆዩና ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ስጋት ያለባቸውን ቤቶች ለመጠበቅና ከፍተኛ ቦሮቦር ለማከም ጥብቅ የደን ሥራዎች ይከናወናሉ።

በኒያባሮንጎ ወንዝ ተፋሰስ ተፈጥሮ ላይ መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎች እንቅስቃሴዎች

SUNCASA | Amharic - Kigali Watershed