Water for the Future staff working on invasive alien species removal on Jukskei river -SUNCASA

የሥርዓተ ጾታ እኩልነትና ማኅበራዊ አካታችነት

የሱንካሳ ፕሮጀክት በድሬ ዳዋ (ኢትዮጵያ)፣ በኪጋሊ (ሩዋንዳ) እና በጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ) ከተሞች በሚካሄዱ  የከተማ ተፈጥሮ ተኮር አጸፋዎች (NbS) ዕቅድ ዝግጅት፣ ትግበራና ክትትል ሥራዎች የሴቶችንና የሌሎች አነስተኛ ውክልና ያላቸውን ቡድኖች ተሳትፎ የማረጋገጥ ዓላማ አለው፡፡

የአየር ንብረትና የብዝኀ ሕይወት ቀውሶች ከሰዎች የገቢና የሥራ ዕድሎች አኳያ የሚያሳርፉት ተጽዕኖ እንደ ጾታና መሰል የማንነት መገለጫዎች ይለያያሉ፡፡ የሥርዓታዊ አግልሎትና አድልዎ ተጠቂ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ብዙውን ጊዜ ተመጣጣኝ ባልሆነ መልኩ ተጎጂ ሲሆኑ ይስተዋላል፡፡ በታሪካዊና ባሕላዊ የሥርዓተ ጾታና ማኅበራዊ ልማዶች ሳቢያ በተፈጥሮ ሃብቶች አጠቃቀምና አስተዳደር ረገድ በሴቶችና ልጃገረዶች እንዲሁም በወንዶችና ወጣቶች መካከል የሚና ልዩነት አለ፡፡

የአየር ንብረትና የብዝኀ ሕይወት ቀውሶች ከሰዎች የገቢና የሥራ ዕድሎች አኳያ የሚያሳርፉት ተጽዕኖ እንደ ጾታና መሰል የማንነት መገለጫዎች ይለያያሉ፡፡ የሥርዓታዊ አግልሎትና አድልዎ ተጠቂ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ብዙውን ጊዜ ተመጣጣኝ ባልሆነ መልኩ ተጎጂ ሲሆኑ ይስተዋላል፡፡ በታሪካዊና ባሕላዊ የሥርዓተ ጾታና ማኅበራዊ ልማዶች ሳቢያ በተፈጥሮ ሃብቶች አጠቃቀምና አስተዳደር ረገድ በሴቶችና ልጃገረዶች እንዲሁም በወንዶችና ወጣቶች መካከል የሚና ልዩነት አለ፡፡

የሱንካሳ ፕሮጀክት ተጽዕኖ አድራሽና ፍትሐዊ ይሆን ዘንድ እነዚህን የሚና ልዩነቶች፣ ኃላፊነቶችና ዕውቀቶች ከግምት እንዲያስገባና በሌላ በኩልም አግላይ ልማዶችና ገቢሮችን እንዲቀርፍ ታስቦ ተነድፏል፡፡ ፕሮጀክቱ የማኅበረሰቡ አባላት ከተፈጥሮ ተኮር አጸፋዎች (NbS) ጋር በተያያዘ በተለይ በወንዶችና በውሳኔ ሰጪ አካላት ዘንድ ለሥርዓተ ጾታ ስሱ የሆኑ አሠራሮች ግንዛቤ እንዲስፋፋ ይሠራል፡፡

ሱንካሳ ማኅበራዊ ልማዶችንና የአካባቢያዊ ሥልጣን ክፍፍልን ጨምሮ በሥርዓተ ጾታ ተኮር እንቅፋቶች ዙሪያ ማኅበረሰባዊ ምክክሮች እንዲካሄዱ አስፈላጊ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ ፕሮጀክቱ ሴቶችም ሆኑ ሌሎች አነስተኛ ውክልና ያላቸውን ቡድኖች ለውሳኔ ሰጪነት ያላቸውን ተደራሽነት ለማሻሻልና በተፈጥሮ ተኮር አጸፋዎች (NbS) እንቅስቃሴዎችና በአካባቢያዊ ደረጃ በማስተዳደር ረገድ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚያስችሉ የበዙ ዕድሎችን ለመፍጠር ይሻል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ሱንካሳ የየከተሞቹ አስተዳደሮች ለሥርዓተ ጾታ ስሱነት ያላቸው የተፈጥሮ ተኮር አጸፋዎች (NbS) ሥልቶችን እንዲነድፉ በማገዝ ይበልጥ አሳታፊ የፖሊሲ አወጣጥ ሒደት እንዲሰፍን አስተዋጽዖ ያደርጋል፡፡

በሥርዓተ ጾታና ማኅበራዊ አሳታፊነት ረገድ የሱንካሳ ግቦች

  • ማኅበራዊ ልማዶችን መገዳደር:- የሴቶችንና ሌሎች አነስተኛ ውክልና ያላቸውን ቡድኖች መብቶች የሚያራምዱ አዎንታዊ ማኅበራዊና ሥርዓተ ጾታዊ ልማዶችን ማበረታታት፡፡
  • ዕድሎችን መፍጠር:- ሴቶችን እና ሌሎች አነስተኛ ውክልና ያላቸውን የማሕበረሰብ አባላት በተፈጥሮ ተኮር አጸፋዎች (NbS) ትግበራ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማስቻልና በውሳኔ መስጫ ቦታዎች ላይ ተደራሽነት ማግኘታቸውን ማረጋገጥ፡፡
  • ድልድዮችን ማበጀት:- የሴቶች አደረጃጀቶችንና ሌሎች አነስተኛ ውክልና ያላቸው የማኅበረሰብ ቡድኖች በአካባቢያቸው በሚተገበሩ ተፈጥሮ ተኮር አጸፋዎች (NbS) አስተዳደር ሒደቶች ላይ ትርጉም ባለው መልኩ ተሳትፎ እንዲኖራቸው መደገፍና ከዚሁ ጎን ለጎንም የየአካባቢው አስተዳደሮች ኃላፊነት ያለባቸው ከመሆኑ አኳያ  ይበልጥ ለሥርዓተ ጾታ እኩልነት ጉዳዮች ስሱነት ያለው የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት እንዲተገብሩ ማገዝ፡፡

ከከተማ ተፈጥሮ ተኮር አጸፋዎች (NbS) አንፃር የ GESI 3 አላባውያን

Graphic - GESI elements in Urban NbS