SUNCASA | SUNCASA volunteers working on afforestation of the Ada Kebele region in Dire Dawa, Ethiopia.

ድሬዳዋ

SUNCASA የጎርፍ አደጋ ስጋትን፣ የአፈር መሸርሸርንና የከተማ ውሃ እጥረትን ለመቅረፍ በድሬዳዋ የደቻቱ ወንዝ ተፋሰስን የማደስ ሥራ የሚያከናውን ይሆናል። ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ከ200,000 በላይ ሰዎች ሥርዓተ-ጾታን ማእከል አድርገውና ተፈጥሮ ላይ ተመሥረተው ከሚወሰዱት የመፍትሔ እርምጃዎች (NbS) ተጠቃሚ የሚሆኑ ሲሆን እኒህም የሚያካትቱት የደን ልማት ማከናወን፣ የተከለሉ የደን ቀጠናዎችን ማቋቋም፣ የጎርፍ ውሃን ለመቆጣጠር እና ዘላቂ የመተዳደርያ ገቢን ለመፍጠር ጥምር የግብርና ደን ልማት፣ እንዲሁም የሙቀት ተጽዕኖዎችን እና ጎርፍን ለመቀነስ የከተማ ዛፍ ተከላን ያካትታል።

የደራሽ ጎርፍ፣ የአፈር መሸርሸር፣ የውሃ እጥረትና፣ የከተማ ሙቀት መጨመር በድሬዳዋ የሚስተዋሉ የአየር ንብረት ለውጥ አሳሳቢ ስጋቶች ናቸው። የከርሰ ምድር ውሃ እየቀነሰ በመምጣቱ የማኅበረሰቡ ጤናና የአካባቢው ኢኮኖሚ፣ የሙቀትና የውሃ እጥረት ስጋት አንዣቦባቸዋል።
 

SUNCASA ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች በሚገኙ የከተማና የገጠር ቀበሌዎች (መንደሮች) ላይ በማተኮር ተፈጥሮን ያማከለ (NbSን) ተግባራዊ ለማድረግ ከአገር ውስጥ አጋሮች ጋር በመተባበር ይሠራል። በSUNCASA ስር የሚተገበሩት (የNbS) ተፈጥሮን ያማከሉ መፍትሄዎች የጎርፍ መጥለቅለቅንና የአፈር መሸርሸርን ይቀንሳሉ፣ የከርሰ ምድር ውሃ ክምችትንና የጥብቅ ደን ጣቢያዎች ልማትን ያሳድጋሉ እንዲሁም የግብርናና ደን ልማት ዕድሎችን በማስፋት የመሬት ምርታማነት፣ የሰብል ምርትና የቴክኖሎጂ ተደራሽነት እንዲሻሻል ያደርጋሉ። 
 

ይህ ዕቅድ በችግኝ አመራረት፣ በንብ እርባታ፣ በመኖ ልማት፣ በኮምፖስት አመራረትና ሌሎች ከፕሮጀክቶች ጋር በተያያዙ ዘርፎች ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠናና የሥራ ዕድል በመፍጠር ከ3,500 እስከ 4,000 ሰዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋል። ፕሮጀክቱ የማኅበረሰብ ፓርኮችን በማልማትና በወል መሬቶች፣ በግል ይዞታዎችና በመንገድ ዳርቻዎች ላይ ዛፎችን በመትከል የከተማ አረንጓዴ ሥፍራዎች እንዲስፋፉ ያበረታታል። 
 

SUNCASA በደቻቱ ወንዝ ተፋሰስ ላይ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች

SUNCASA | Amharic - Dire Dawa Watershed